3ተኛው አመታዊ የናይል ወንዝ ፍትሀዊ ተጠቃሚነትና ቀጠናዊ ትስስር ኮንፍረንስ በአ.አ በመካሄድ ላይ ነው።

“የጋራ ሀብት ለጋራ መጻኢ ጊዜና ለጋራ ብልጽግና” በሚል መሪ ቃል በውጭ ጉዳይ ኢንስቲቲዩት፤በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና በውሀና ኢነርጂ ሚኒስቴር  አዘጋጅነት  ኮንፈረንሱ እየተካሄደ ይገኛል።

በመድረኩ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አረጋን ጨምሮ የውሀና ኢነርጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ረሰ ኢ/ር ሱልጣን ወሌ፤ የውጭ ጉዳይ ኢንስቲቲዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ጃፋር በድሩ፤ የናይል ተፋሰስ አገራት ተወካዮች፤ የኢትዮጵያ የሲቪል ማህበራት ተወካዮችና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ታድመዋል።

መድረኩ በናይል ወንዝ ፍትሀዊ ተጠቃሚነትና በተፋሰሱ አገራት መካከል ስለሚኖር ትብብርና ቅንጅታዊ አሰራር ላይ ይመክራል ተብሎ ይጠበቃል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *