ሚያዝያ 21 ቀን 2016 ዓ.ም የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር የተከበሩ አቶ ጃፋር በድሩ ከውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ኢንጂነር ዶ/ር ሃብታሙ ኢተፋ ጋር በጋራ ሊሰሩባቸው በሚችሉባቸው ጉዳዮች ላይ ተወያዩ ፡፡
ክቡር አቶ ጃፋር በድሩ ኢንስቲትዩቱ ከሚንስቴር መስሪያ ቤቱ ጋር በመቀናጀት በምርምር እና ጥናት ውጤቶች እንዲሁም በአቅም ግንባታ ስልጠናዎች ዙሪያ በጋራ ሊሰሩ እንደሚችሉ ያስረዱ ሲሆን አያይዘውም እንደ አፍሪራን አይነት ትላልቅ አገራዊ ኮንፍረንሶችን ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ጋር በጋራ መስራቱ ውጤታማ እንደሚሆን ገልጸዋል፡፡

ክቡር ሚኒስትሩም እንደ ሃገር ሁለቱም ተቋማት ትልቅ ሃገራዊ ተልዕኮን ለማሳካት የበኩላቸውን ሚና እየተወጡ መሆኑን ገልጸው አሁን የተጀመረው በጋራ የመስራት ስምምነት ሁለቱን ተቋማት ይበልጥ እንደሚያስተሳስር እና ስራውንም እንደሚያጠናክረው ገልጸዋል፡፡
አያይዘውም በዚህ አመት የሚካሄደው 3ኛው የአፍሪራን ኮንፈረስ (The 3rd AFRI-RUN Conference) ቅድመ ዝግጅት ላይ ተወያይተዋል፡፡
እንደሚታወቀው የዚህ ኮንፈረንስ አጠቃላይ አላማ የአፍሪካን ድንበር ተሻጋሪ የውሃ ሀብቶች ፍትሃዊ እና ምክንያታዊ በሆነ መንገድ የመጠቀም መርህን በመጠቀም መዋቅራዊ ለውጥ ማምጣት፤ የአፍሪካን ብልፅግና እውን ለማድረግ በአህጉሪቱ ያሉ የወሰን ተሻጋሪ የውሃ ሃብት አስተዳደርና አጠቃቀምን መልካም ተሞክሮዎችን ለማጉላት መሆኑ ይታወቃል።
ከዚህ ቀደም የነበሩትን የአፍሪራን ኮንፍረንሶች የውጪ ጉዳይ ኢንስቲትዩት፣ የውጪ ጉዳይ ሚንስቴር እና የውሃና ኢነርጂ ሚንስቴር በጋራ በማዘጋጀት ከተፋሰሱ ሃገራት ከሚመጡ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት እና ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር የምክክር መድረክ እንዳዘጋጁ ይታወቃል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *