“የሁለት ውኃዎች ዐቢይ ስትራቴጂ” በሚል ርእስ  በአብርሆት ቤተ መጸኀፍት የምረቃ ስነስርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የውጪ ጉዳይ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር የተከበሩ አቶ ጃፋር በድሩ

መፅሃፉ ኢትዮጵያን ወደ ብልጽግና ለማድረስ ለሚደረገው ሀገራዊ ጥረት የጋራ ርብርብ ማዕከሎችን ይለያል፤ የአባይ ተፋሰስና የቀይ ባህር ቀጠና እንደአይን ብሌናችን የምናያቸው ቁልፍ የብሄራዊ ደህንነታችን ጉዳዮች እንደሆኑ ያስቀምጣል፤ ወደ ቀይ ባህር ለመመለስና የባህር በር ባለቤትነትን ለማግኘት የሚደረገው ጥረት የሚያግዙ ስትራቴጂዎችን ያስቀምጣል፤  ከጎረቤት ሃገራት ጋር በሰጥቶ መቀበል መርህ ትብብርን በማሳደግ አብሮ ማደግና አብሮ መልማት የሚቻልባቸው መንገዶችን በመለየት የባህር በር ፍላጎታችንን ለማሟላት ይተልማል በማለት ያስረዱ ሲሆን

አያይዘውም ትልቁ ጉዳይ አንዱ የሚጎለውን ከሌላው ጋር በወዳጅነት የሚሞላበት ፎርሙላ ማግኘት ላይ ነው። በአንዱ ሃገር ያሉ ሃብቶች በሌላው አለመኖራቸው በቀንዱ ሃገራት መካከል ለመተባበርና ሃብትን በጋራ ለመጠቀም ትልቅ እድል የሚሰጥ መሆኑን እና የቀንዱ ሃገራት ከተባበርንና ለመተሳሰር የሚያስፈልጉ መሰረተ-ልማቶችን መዘርጋት ከቻልን ቀጠናው ከግጭት አዙሪት እየወጣ ወደ ልማትና ትስስር ቀጠና የመቀየር ሰፊ እድል ያለው መሆኑን ገልጸዋል::

በመጨረሻም የዚህ መጽሃፍ ዝግጅት ታሪክ በችግር ውስጥ ሆኖ የተሻለ ጊዜን ማሰብ፤ ስለ ቀጣዩ የተሻለ ጊዜ መዘጋጀት ወሳኝ መሆኑን የምንማርበት ነው ሲሉ ገልጸዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *