ዲፕሎማሲያችን ለብሄራዊ ጥቅማችን በሚል መሪ ቃል በሳይንስ ሙዚየም የኢትዮጵያ ዲፕሎማሲ አውደርዕይ ጉብኝት አሁንም ተጠናክሮ እንደቀጠለ ነው፡፡
ጥር 13 ቀን 2016 ዓ.ም በሳይንስና ሙዚየም የኢትዮጵያ ዲፕሎማሲ አውደርዕይን ሲጎበኙ ካገኘናቸው መካከል አቶ ዘውዱ አበበ አንዱ ናቸው፡፡ አቶ ዘውዱ አበበ በግብርና ሚኒስቴር ለ36 ዓመት ያገለገሉና አሁን በጡረታ ላይ የሚገኙ ናቸው፡፡
ጉብኝቱን በተመለከተ ደስተኛ ሆነው ሁሉንም መጎብኘታቸውን ጠቁመው የተዘጋጀው አውደርዕይ ከሜዳ እንዳይቀር ከተፈለገ ጉዳዩ በሚመለከታቸው የውጭ ጉዳይ ባለሙያዎች በመጽሐፍ ታትሞ በትርፍ ሳይሆን ወጪዉን ብቻ በመሽፈን ለገበያ ቢቀርብ ህብረተሰቡ መጸሀፉን በማንበብ ሃገሩን እንዲውቅ ቢደረግ የሚል ምክረ ሃሳብ አቅርበዋል። ከጎበኟቸው መካከል የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ እንዴት እንደተቀረጸ እና እንዴት እንደተጀመረ ፣ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርን ከመጀመሪያው ጀምሮ እስካሁን በአመራርነት የመሩት አመራሮች እና ከንግስት ዘውዲቱ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ ያለው የዲፕሎማሲ ግነኙነት ምን እንደሚመስል በፎቶግራፍ በማስደገፍ መቅረቡ ጥሩ ተሞክሮ መሆኑን ተናግረዋል።
አቶ ዘውዱ የቀረበው አውደርዕይ ትልቅ እውቀት በመሆኑ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ለሃገሩ አምባሳደር መሆኑን አውቆ በጉብኝቱ እንዲሳተፍና ሃገራችን የደረሰችበትን የዲፕሎማሲ ደረጃ እንዲያውቅና እንዲረዳ ስል መልእክቴን አስተላልፋለው ብለዋል፡፡