የአዲስ አበባ የስራ አመራር ልህቀት አካዳሚ አመራሮችና ሰራተኞች ከኢንስቲትዩቱ ጋር የልምድ ልውውጥ አደረጉ ፡፡

ጥር 09 ቀን 2016 ዓ.ም የአዲስ አበባ የስራ አመራር ልህቀት አካዳሚ አመራሮችና ሰራተኞች ከውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት ጋር የልምድ ልውውጥ አድርገዋል፡፡

በልምድ ልውውጡም ከኢንስቲትዩቱ መመስረት እስከ አሁን ያለበትን የስራ እንቅስቃሴን ፣ በተቋሙ እየተከናወኑ የሚገኙ የምርምር ስራዎች  በውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት ዋና ዳሬክተር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሰናይ ጌታቸው አቅርበዋል ፡፡ ለአብነትም ካቀረባቸው ውስጥ  የመወያያ ርዕሰ ጉዳይ መፍጠር፣ የፖሊሲ አማራጮችንና ምክረ ሃሳቦችን ማቅረብ፣ የውጭ ግንኙነት ሰራተኞችን ማፍራት እና የተበታተኑ የዲፕሎማሲ ስራዎችን ወደ አንድ ቋት ማምጣት የሚሉትን እና መሰል ተግባራትን ኢንስቲትዩቱ እየሰራ እንደሚገኝ አስረድተዋል፡፡

የልህቀት አካዳሚው ሰራተኞችና አመራሮች በልምድ ልውውጡ ግልጽነት እንዲፈጠርላቸው የፈለጉትን ጥያቄዎችና ሃሳቦች አቅርበው በኢንስቲትዩቱ ተመራማሪዎችና እና የዋና ዳይሬክተር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሰናይ ምላሽ ተሰጥቶባቸው በቀጣይ በሚሰሯቸው የጥትና ምርምር ስራዎች በጋራ ለመስራት የመግባቢያ ሰነድ አዘጋጅተው እንደሚመጡ አቅጣጫ አስቀምጠዋል፡፡

በመጨረሻም ኢንስቲትዩቱ እየሰራቸው የሚገኙ የምርምር ስራዎችን በመጎብኘት ውይይቱ ተጠናቋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *