አዲስ አበባ፣ ጥር 10/ 2016 ዓ.ም


የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አመራሮችና ሠራተኞች በሳይንስ ሙዚየም የተከፈተውንና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ጋር በመተባበር ያዘጋጁትን አውደርዕይ ጎብኝተዋል።

በጉብኝቱ ወቅት ሀገራችን ኢትዮጵያ በአህጉራችን አፍሪካ እና በአለም አቀፍ መድረክ የረጅም ጊዜ የዲፕሎማሲ ልምድ እንዳላት በዘርፉ ባለሙያዎች ሰፊ ገለጻ ተደርጓል።

ኢትዮጵያ ከአፍሪካ መዲናነት እስከ ዓለም መድረክ ተደማጭና ተጽዕኖ ፈጣሪ እንድትሆን ለማስቻል ብሎም ብሔራዊ ጥቅሟን ለማስጠበቅ የተጓዘችውን የዲፕሎማሲ ርቅት ከአውደርዕይው ለመገንዘብ ተችሏል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *