የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፕሬዝዳንት ክብርት ሣህለወርቅ ዘውዴ የኢትዮጵያ የዲፕሎማሲ ሳምንት አውደ ርዕይን በይፋ ከፈቱ


(ጥር 02 ቀን 2016 ዓ.ም. አዲስ አበባ): የኢ.ፌ.ዲ.ሪ.ፕሬዝዳንት ክብርት ሣህለወርቅ ዘውዴ ” “ዲፕሎማሲያችን ለብሔራዊ ጥቅማችን” በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀውን የኢትዮጵያ የዲፕሎማሲ ሳምንት አውደ ርዕይን በሳይንስ ሙዚየም በይፋ ከፈቱ።

ክብርት ፕሬዝዳንቷ የዲፕሎማሲ ሳምንት አውደ ርዕዩን በይፋ የከፈቱት ከኢ.ፌ.ዲ.ሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክቡር አቶ ደመቀ መኮንን እና ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት ፣መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ያደረጉ የዲፕሎማሲ ማኀበረሰቦች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ነው።

የዲፕሎሲ ሳምንቱ ዋና ዓላም የኢትዮጵያን የዲፕሎማሲ ታሪክ ፣ወቅታዊ የዲፕሎማሲ ድሎች እና የመጪው ዘመን ዲፕሎማሲ አቅጣጫ ለማመላከት ታሳቢ ያደረገ ነው።

የዲፕሎማሲ ሳምንት እስከ ጥር 24 ቀን 2016ዓ.ም. ድረስ ለጎብኝዎች ክፍት ይሆናል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *