ታህሳስ 23/2016 ዓ.ም  የውጭ  ጉዳይ ኢንስቲትዩት  እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር  በጋራ “የኢትዮጵያ  የምስራቅ አፍሪካ  ኮሚኒቲ  አባላት  ፍላጎት  እና ትኩረት  የሚሹ ጉዳዮች’’  በሚል ርዕሰ የጋራ የፖሊስ  ምክክር መድረክ አዘጋጁ ።

የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ጃፋር በድሩ በመድረኩ ንግግር ያደረጉ ሲሆን ኢትዮጵያ በፍጥነት እያደገ ያለ ኢኮኖሚ፣ የበለጸገ የተፈጥሮ ሃብትና የሰው ሃይል ባለቤት እና ሰፊ የገበያ ዕድል ያላት ሃገር እንደመሆኗ ዕድገቷን ለማፋጠን እና  አስተማማኝና ቀጣይነት ያለው  ልማት  ለማረጋገጥ  ከመቸውም በላይ ጠንካራ መሰረት ያላቸው ዓለማቀፋዊ፣ አህጉራዊ እና ቀጠናዊ የኢኮኖሚ እና ንግድ ትብብሮች እንደሚያስፈልጋት ገልጸው በዚህ ረገድ  በአፍሪካ አህራዊ ነጻ የንግድ ቀጠና  ዕቅድ እና በBRICS  ማዕቀፍ  ተጠቃሚ ለመሆን እየተደረጉ ያሉ ሃገራዊ ጥረቶች  ተስፋ የሚጣልባቸው መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡ 

የመድረኩ አላማ የኢትዮጵያ የምስራቅ አፍሪካ ኮሚዩኒቲ (EAC) አባል መሆን የሚያስገኘውን ጥቅም በውል ለመለየት፣ አባል ለመሆን ያላትን ዝግጁነት ለመረዳት፣ እንዲሁም ሃገራችን አባል ብትሆን ተከትለው ሊመጡ የሚችሉ በተለይ ከኢጋድ ህልውና እና መጠናከር ጋር ተያይዞ ተገማች የሆኑ ተግዳሮቶችን ለመለየት መሆኑን ዋና ዳይሬክተሩ አያይዘው ገልጸዋል፡፡

በምክክር መድረኩ አራት የመወያያ ጽሁፎች ቀርበው ውይይት የተደረገባቸው ሲሆን  በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነትና ሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ ዶ/ር ዲማ ነገዎን ጨምሮ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት  ቋሚ ኮሚቴ አባላት፣ የመከላከያ ሰራዊት አመራሮችና መኮንኖች፣ አምባሳደሮች፣ ዲፕሎማቶች፣ ዳይሬክተር ጀነራሎች፣ የተለያዩ ተቋማት የስራ ሃላፊዎች እንዲሁም የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር መስሪያ ቤት ሰራተኞች እና የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት ተመራማሪዎችና የስራ ኃላፊዎች በመድረኩ ተሳተፊ መሆናቸው ታውቋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *