በኢትዮጵያ የዲፕሎማሲ ታሪክ ላይ ያተኮረ የዲፕሎማሲ አውደ ርዕይ በቀጣይ ሳምንት ይጀመራል” – አምባሳደር መለስ ዓለም(ዶ/ር)


በኢትዮጵያ የደለበ የዲፕሎማሲ ታሪክ እና በወቅታዊ የሀገሪቱ የዲፕሎማሲ ስኬቶች ላይ ያተኮረ የዲፕሎማሲ አውደ ርዕይ በቀጣይ ሳምንት እንደሚጀመር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ ዓለም (ዶ/ር) ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ የኢትዮጵያ ዲፕሎማሲ ሳምንት ከጥር 02 ቀን እስከ ጥር 24 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ ይካሄዳል።

የአውደ ርዕዩ ዓላማ የኢትዮጵያን የረጅም ጊዜ የዲፕሎማሲ ታሪክ በማሳየት አገራችን በአፍሪካ፣ የአፍሪካ ቀንድ እና በዓለም አቀፍ መድረኮች የተጫወተቻቸውን ሚና ማሳየት አንዱ መሆኑን ቃል አቀባዩ ገልጸዋል።

ወቅታዊውን የአገራችን የባለብዙ ወገንና ሁለትዮሽ የዲፕሎማሲ እንቅስቃሴ ስኬትና ተግዳሮቱን ማሳየት፣ በዚህም ህብረተሰቡ ደጋፊ እንዲሆን ማስቻልም ሌላው ዓላማው ነው ብለዋል።

በዲፕሎማሲ ሳምንቱ ላይ አሁን ካለንበት የዲጂታል ዘመን አንፃር የአዲሱ ዘመን ዲፕሎማሲን በመጠቀም ኢትዮጵያ ያላትን የዲፕሎማሲ ወረት በመጠቀም የበለጠ ተደማጭ ለመሆን እያደረገችው ያለውን እንቅስቃሴ ማመላከትም የአውደ ርዕዩ ዓላማ መሆኑን አምባሳደር ዶ/ር መለስ ጠቅሰዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *