የፈረንሳይ ሚሲዮን ምክትል መሪ ሚስተር ክላውደ በውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት በመገኘት ውይይት አካሄዱ፡፡
ህዳር 10,2016 ዓ.ም የፈረንሳይ ሚሲዮን ምክትል መሪ ሚስተር ክላውደ በውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት የኤዢያና ፓስፊክ ዳይሬክተር ከሆኑት ከዶ/ር ዳርዕስከዳር ታዬ እና የውጭ ግንኙነት የስልጠናና ፖሊሲ ማማከር  ዳይሬክተር ከሆኑት ከዶ/ር ተስፋዬ በዛብህ ጋር ውይይት አድርገዋል።
በውይይታቸው ስለ ኢንስቲትዩቱ አጠቃላይ ገለጻ የተደረገላቸው ሲሆን ሚስተር ክላውድ በበኩላቸው በሚኒስቴር መስሪያቤታቸው  ውስጥ ስለሚገኝ የዲፕሎማቶች ማሰልጠኛ በዝርዝር አስረድተዋል፡፡
አያዘውም ፈረንሳይ በፕሮቶኮል ከፍተኛ ልምድ ያላት ሀገር መሆኗን አስታውሰው በዚህ ርእሰ ጉዳይ እንዲሁም  በስልጠና ዘርፍ፣ በምርምር ዘርፍ፣ የጋራ ኮንፍረንሶችን ለማካሄድ እና በተመረጡ ጉዳዮች ላይ public lecture ለማድረግ ከኢንስቲትዩቱ ጋር በጋራ ሊሰሩ እንደሚችሉ ተናግረዋል፡፡
በመጨረሻም አሁን የተጀመሩትን የጋራ ስራዎች በተጠናከረ መልኩ ለማስቀጠል ሁለቱም ተቋማት በጋራ እንደሚሰሩ ገልጸዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *