በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክቡር አቶ ደመቀ መኮንን የተመራ ከውጭ ጉዳይ ሚንስቴር የተውጣጣ የልዑካን ቡድን የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩትን ጎበኙ።

በጉብኝቱ ወቅት ለሀገራችን የዲፕሎማሲ ስኬት በኢንስቲትዩቱ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን ለክቡር ሚኒስትሩ ገለፃ የቀረበላቸው ሲሆን ክቡር ሚኒስትሩ በኢንስቲትዩቱ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን ያደነቁ ሲሆን በተለይም ምቹ የስራ አካባቢን ከመፍጠር እና ስራን በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ በማገዝ ውጤታማነትን እና ጥራትን ከማላቅ አንፃር እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ወደ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሊስፋፉ እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡ በተጨማሪም ክቡር ሚኒስትሩ በቀጣይ ኢንስቲትዩቱ ትኩረት ሰጥቶ ከሚንስቴር መስሪያ ቤቱ  ጋር በጋራ ሊሰራባቸው የሚገቡ ጉዳዮች ላይ አቅጣጫ አስቀምጠው ጉብኝቱ ተጠናቋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *