መርሃ-ግብሩን ያስጀመሩት የውጪ ጉዳይ ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ መሳፍንት ተፈራ ሲሆኑ  ሰላም ለሀገር ግንባታ ወሳኝ መሆኑን እና በዚህ በሰላም ግንባታ ሴቶችን ማሳተፍ ሚናው ከፍተኛ መሆኑን በዝርዝር አስረድተዋል።
በፕሮግራሙ ላይ ክብርት አምባሳደር ዶ/ር ትዝታ ሙሉጌታ እና ዶ/ር ሳሙኤል ተፈራ  የሴቶች ሁለንተናዊ  ተሳትፎ እና  ለሰላም ያለቸው ሚና እንዲሁም ሴቶች ሥነ-ምግባርን የተላበሰ ትውልድን በማነፅ ለሰላም ያላቸው ሚና በሚመለከት ጥናታዊ ፅሑፎቻቸውን አቅርበዋል ። በቀረቡት ፅሑፎች  ላይ  ውይይት  ተደርጓል። በመጨረሻም  ስለ ሰላም አስፈላጊነት የሚገልፅ  የስነ-ጥበብ ስራ በፕሮግራሙ የቀረበ መሆኑ ታውቋል።

By admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *