የፌደራል መንግስት የፖሊሲና የምርምር ተቋማት   የፖሊሲ ጥናት የጋራ መድረክ አቋቋሙ፡

የፖሊሲ ጥናት የጋራ መድረኩ ነኀሴ 24/2015 ዓ.ም ሁለት ዩኒቨርሲቲዎችን እና ስምንት የምርምር ተቋማት እንዲሁም የኢትዮጵያ የአመራር ልህቀት አካዳሚ፣ የኢትዮጵያ ስታትስቲክስ እና የኢትዮጵያ ዲያስፖራ አገልግሎት በአጠቃላይ 13 የፌደራል መንግስት የፖሊሲና ምርምር ተቋማትን በማካተት በውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት ሁሉም  አባላቱ በተገኙበት ተቋቁሟል፡፡

የመድረኩ አላማም ትስስር መፍጠር እና እውቀትን መጋራት እንዲሁም የምርምር ተቋማቱ በቅንጅት በመስራት ከተጫባጭ አካባቢያዊ እና ሀገራዊ ዓላማ አንጻር በማህበራዊ፣ በኢኮኖሚያዊ፤ በፖለቲካዊ፣ አካባቢያዊ እና ቀጠናዊ ጉዳዩች አገራችን ኢትዮጵያ ማስመዝገብ ያለባትን እንዲሁም መጫወት ያለባትን ሚና በጥናትና ምርምር አስደግፎ ለፖሊሲ አውጪ፣ ለፖሊሲ አስፈጻሚ፣ እና ለሕግ ተርጓሚ ማቅረብ እና በአህጉራዊ እና ዓለማቀፋዊ መድረክ የአገርን ዘላቂ ብሔራዊ ጥቅም በትውልድ ቅብብሎሽ እንዲከበር፣ ተቀናጅተው እንዲሰሩ ለማድረግ ከፍ ያለ ፋይዳ ያለው መሆኑ ከመድኩ ተገልጿል፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *