የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት የስልጠናና ማማከር ዳይሬክቶሬት በውጭ ጉዳይ ሚንስቴር  አዲስ የስራ ስምሪት ለተመደቡ 117 ለሚሆኑ ድፕሎማቶች እና የአስተዳደር ዘርፍ ሰራተኞች ለ 6 ቀናት የቆየ የአቅም ግንባታ ስልጠና  ሰጠ፡፡
ስልጠናው ኢትዮጵያ ከውጭ ሃገራት ጋር በሚኖራት ዲፕሎማሲያዊ  ግንኙነት የዲፕማቶች ሚና ምን መምሰል እንዳለበት የቀረበ ሲሆን የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር እንዲሁም የቱሪዝም ኢንዱስትሪን ለማስፋፋት በሚደረገው ሃገራዊ እንቅስቃሴ ዲፕሎማቶች ስለሚኖራቸው ሚና በዝርዝር ቀርቧል፡፡
ሰልጣኞች ከስልጠናው በተጨማሪ ከነባር አምባሳደሮች እና ዲፕሎማቶች የልምድ ልውውጥ እንዲያገኙ ተደርጓል፡፡
በነበረው የልምድ ልውውጥ ክብርት አምባሳደር ብርቱካን አያኖ ፣ክቡር አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ፣ የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ደሳለኝ አምባው እና የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር እና የስልጠና እና ማማከር ዳይሬክተር አቶ መሳፍንት ተፈራ የተገኙ ሲሆን የስልጠናውን የስራ መመሪያ በመስጠት የመዝጊያ ንግግር ያደረጉት ክቡር አምባሳደር ምስጋኑ አረጋ  ሰልጣኞች ብቁ እና ፕሮፌሽናል ዲፕሎማት መሆን እንደሚጠበቅባቸው ገልጸው ወገንተኝነታቸው ሁሌም ለሃገር እና ብሄራዊ ጥቅምን ያሰቀደመ መሆን እንዳለበት አሳስበዋል ፡፡ በአስተዳደር ዘርፍም የሰለጠኑ ባለሙያች በዘርፉ ብዙ መስራት  እንደሚጠበቅባቸው  ገልጸዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *