የኢትዮጵያ የዳስፖራ አገልግሎት አመራሮች የዉጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩቱን ጎበኙ
ነሐሴ 11/2015 ዓ.ም በዶ/ር መሐመድ ኢድሪስ የተመራ 6 አባላት ያሉት የኢትዮጵያ ዲያስፖራ አገልግሎት የማናጅመንት ቡድን የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት የስራ እንቅስቃሴን የጎበኙ ሲሆን የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን መሰረት ልማት ዝርጋታ እና ምቹ የስራ ቦታ ከመፍጠር አንጻር የተሰሩ ስራዎችን ጎብኝተዋል፡፡በ2015 ኢንስቲትዩቱ ያስመዘገባቸውን ከፍተኛ አፈጻፀሞች ላይ እንዲሁም ኢንስቲትዩቱ በቀጣይ ሊሰራባቸው የለያቸውን የትኩረት መስኮች ላይ ገለፃ የተሰጠ ሲሆን ዶ/ር ደሳለኝ አንባው እና አቶ ጃፋር በድሩ እንግዶቹን ተቀብለው አስተናግደዋል፡፡
