ነኀሴ 18/2015 ዓ.ም የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት የ2015 በጀት አመት እቅድ የስራ አፈጻጸም ሪፖርት እና የ2016 በጀት አመት እቅድን ተመለከተ፡፡

የ2015 በጀት አመት የእቅድ ስራ አፈጻጸም ክንውኑን የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት የስትራቴጂያዊ ጉዳዮች ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ጥሩዘር ሰይፉ ለተቋሙ ሰራተኞች አቅርበዋል::  በሪፖርቱ በዋናነት በጥናትና ምርምር ዘርፍ : በፓሊሲ ምክክር :  በዲፕሎማሲ ስልጠና እና እንዲሁም በአጋርነት እና ትስስር  ዘርፍ የተሰሩ ስራዎች በዝርዝር የቀረቡ ሲሆን በነበረው በጀት አመት የነበሩ ጥንካሬዎች እና ድክመቶች  ተለይተው ቀርበዋል :: 

የስራ አፈጻጸም ሪፖርቱን የኢንስቲትዩቱ የበላይ አመራሮች  ከተቋሙ ሰራተኞች ጋር በጋራ የገመገሙት ሲሆን በግምገማውም  የስራ አፈፃፀም ሪፖርቱ  ከእቅዱ አንፃር ስኬታማ እንደነበር የገለጹት የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ደሳለኝ አምባው ሲሆኑ በ2015 የታዩ ድክመቶች በቀጣይ በጀት አመት ጥሩ ማስተማሪያ እንደሚሆኑ እና የአፈፃፀም ግምገማም ዋናው አላማ ለቀጣይ ስራ ልንማማርባቸው የምንችላቸውን ክንውኖች ማጉላት እንደሆነ ገልፀዋል :: 

የኢንስቲትዩቱን የ2016 በጀት አመት እቅድ  የዋና ዳይሬክተር ፅ/ቤት ሓላፊ አቶ ሰናይ ጌታቸው ያቀረቡ ሲሆን በመጨረሻም እቅዱን የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ደሳለኝ አምባው ከዘርፍ አመራሮች እና ሓላፊዎች ጋር በመፈራረም አፅድቀዋል::

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *