የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሰራተኞች እና የተጠሪ ተቋማት ሰራተኞች በጋራ በመሆን አረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሀ ግብር በ እይ ሲቲ ፓርክ አካሄዱ።
መርህ ግብሩን ያስጀመሩት ከኢ.ፌ.ዲ.ሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አምባሳደር እሸቴ ጥላሁን ሲሆኑ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የሁለተኛውን ምዕራፍ ” ነገን ዛሬ እንትከል ” በሚል መሪ ቃል ያቀረብት ሐገራዊ ጥሪ ተከትሎ ፣ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሌሎች ተጠሪ ተቋማት የስራ ሃላፊዎችና ዲፕሎማቶች አስር ሺህ ችግኞችን በመትከል ለአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር ድጋፋችንን በተግባር ለመግለጽና የራሳችንን አሻራ ለማሳረፍ መሆኑን ገልፀው የዚህ ታሪካዊ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብራችን በአፍሪካ ቀንድ ለሚከሰተው ተደጋጋሚ ድርቅና ርሃብ፣ እንዲሁም በግጦሽ መሬትና በውሃ ሃብት እጥረት የሚፈጠረውን ግጭት ለማስወገድ እየታመነበት በመሆኑ የጎረቤት ሀገራት ይህን በጎ ተሞክሮ እየተጋሩ እንደሚገኙ አስረድተዋል። እያይዘውም ይህ መርኃግብር ከሀገራቱ ጋር ለሚኖረን ሁለንተናዊ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት መጠናከር የራሱን አስተዋጽዖ ማድረጉን እና በመጨረሻም በዲፕሎማሲው መስክ በስፉት ጥቅም ላይ በመዋል ለሀገራችን በclimate finance ና በካርቦን ትሬዲንግ የተሻለ ተጠቃሚነት ለማስገኘት በጥልቀት መንቀሳቀስ የሚገባን መሆኑን አሳስበዋል ። በተመሳሳይም በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚንስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ እና ከሚንስቴር መስሪያ ቤቱ የተውጣጡ ሰራተኞች እና ከተጠሪ ተቋማት አመራሮች እና ሰራተኞች ጋር በጋራ በመሆን በሐረሪ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሰንፊል በሚባል ቦታ በመገኘት የሐምሌ 10 / 2015 ዓ.ም የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብሩን አከናውነዋል።








