የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት ኃላፊዎች እና ሠራተኞች የ2015 ዓ.ም አረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብርን በእሬቻ የህዝብ መናፈሻ ቦታ በተሳካ ሁኔታ አከናወኑ፡፡

የተተከሉት ችግኞች ለምግብነት የሚውሉ የተለያዩ አይነት ፍራፍሬዎች  ሲሆን  ይህም በዘንድሮ አመት ለምግብነት የሚውሉ ችግኞች ላይ ትኩረት እንዲሰጥ በተቀመጠው አቅጣጫ የተከናወኑ  መሆኑ ታውቋል፡፡
መርሃ-ግብሩን ያስጀመሩት በውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት የዋና ዳይሬክተር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሰናይ ጌታቸው ይህ የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ  መርሃ-ግብርን ታሪክ ለማስቀጠል የሁሉም ኃላፊነት መሆኑን ገልጸው ታሪክ ለመስራት ሁሉም ከልቡ በቅንነት መሳተፍ እንደሚኖርበት ተናግረዋል፡፡
የሁለተኛው ምዕራፍ እና የ2015 ዓ/ም የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ  መርሃ-ግብር “ነገን ዛሬ እንትከል” በሚል መሪ ቃል  በመላው ሀገራችን እየተከበረ የሚገኝ ሲሆን በቀጣይ አራት አመታት 25 ቢሊየን ችግኝ ለመትከል በመንግስት መታቀዱ ይታወቃል ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *